source
stringlengths
4
528
target
stringlengths
3
393
source_lang
stringclasses
1 value
target_lang
stringclasses
1 value
When the protests began the students’ main demand was the complete halting of the Masterplan.
ተቃውሞው ሲጀምር የተማሪዎቹ ዋነኛ ጥያቄ ማስተር ፕላኑ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ መሆን ነበር፡፡
English
Amharic
In May 2014, the government did momentarily halt the plan in order to abate the protests after at least nine were killed and hundreds of ethnic Oromo students were imprisoned.
በግንቦት ወር 2006 መንግሥት ቢያንስ በዘጠኝ ሰዎች ሞት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከታሰሩ በኋላ ፕላኑን ለጊዜው አቋርጦታል፡፡
English
Amharic
But when the government decided to resume plans to implement the Masterplan in November this year resentment boiled over again, resulting in the currently two-week-old student protest leaving at least ten people dead and many injured.
ነገር ግን ማስተር ፕላኑን በተግባር የማዋል ዕቅዱን መልሶ ለመቀጠል መንግሥት ባለፈው ኅዳር ወር ሲወስን ቁጣው በድጋሚ አገርሽቶ ሁለት ሳምንታት የዘለቀ የተማሪዎች ተቃውሞ በመቀስቀስ ቢያንስ ዐሥር ሰዎች ሞተው ብዙዎች ተጎድተዋል፡፡
English
Amharic
Since the highly contested 2005 national election, forceful evictions and urban land grabbing have become frequent in Addis Ababa.
በአወዛጋቢ ሁኔታ ከተጠናቀቀው ምርጫ 97 ወዲህ ብዙ ማፈናቀሎችና የከተማ መሬት መቀራመቶች በአዲስ አበባ ተደጋጋሚ ክስተቶች ሆነዋል፡፡
English
Amharic
The capital city’s rapid growth has resulted in increasing pressure to convert rural land for industrial, housing, infrastructure, or other urban use.
የዋና ከተማዋ ፈጣን ዕድገት የገጠሩን መሬት ለኢንዱስትሪ አገልግሎት፣ ለቤት ሥራ፣ ለመሠረተ ልማትና ሌሎችም የከተማ ፍላጎቶች የማዋሉን ዝንባሌ ጨምሮታል፡፡
English
Amharic
Diaspora-based advocates say the unrest in Oromia is just a part of the general unhappiness that prevails in the country.
ዳያስፖራ አራማጆች ተቃውሞው በአገሪቱ የተንሰራፋው ጠቅላላ ብሶት ውጤት ነው ይላሉ፡፡
English
Amharic
They accuse the government of working for the benefit of a few people at the expense of others.
መንግሥት ለጥቂቶች ጥቅም ብዙኃኑን መስዋዕት እያደረገ ነው በማለት ይወነጅሉታል፡፡
English
Amharic
They even suggest that the Ethiopian government covertly encouraged informal settlement on the outskirts of Addis Ababa so that they could later find a way to intervene under the guise of rebuilding the slums and lease the land to real estate developers.
ከዚያም አልፎ መንግሥት ሆነ ብሎ ሕገ-ወጥ ሰፋሪዎችን በአዲስ አበባ ዳርቻዎች በማበረታታት ኋላ ላይ በአካባቢው የሪል ኢስቴት አልሚዎችን እና የጋራ መኖሪያ ቤት ገንቢዎች የሚሠማሩበትን አጋጣሚ ለመፍጠር ይሠራልም ይላሉ፡፡
English
Amharic
Ermias Legesse, a high profile government defector, traces the cause of the Oromo student protest to events that took place 15 years ago. In his book, Addis Ababa: The Abandoned City, Ermias notes that since 2000 the Addis Ababa city municipality, with the support of the federal government, enacted five different pieces of legislation to legalize” the informal settlements, and then sold the legalized” lands to private property developers.
ኤርሚያስ ለገሰ፣ አሁን የከዳ የመንግሥት ባለሥልጣን ነበር፣ አዲስ አባባ፤ ባለቤት የሌላት ከተማ” ባለው መጽሐፉ ውስጥ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞን 15 ዓመት ወደኋላ ጀምሮ ያስታውሳል፡፡
English
Amharic
Released under Creative Commons. Despite recording double-digit economic growth in recent years, Ethiopia is in serious need of food aid.
ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ካስመዘገበችው የሁለት አሐዝ የኢኮኖሚ ዕድገት በተቃራኒ ከፍተኛ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋታል፡፡
English
Amharic
Observers consider the current food crisis to be the worst in thirty years, similar to the famine of 1984-85, which led to thousands of deaths.
ታዛቢዎች እንደሚሉት የአሁኑ የምግብ ቀውስ በሠላሳ ዓመታት ውስጥ የከፋው ሲሆን የብዙ ሺሕዎችን ነፍስ ከቀጠፈው ከ1977ቱ ረሀብ ተመሳሳይ ነው፡፡
English
Amharic
According to a report by the U.N. Office for the Coordination of Humanitarian Affairs the number of relief food beneficiaries in Ethiopia has increased to 4.5 million people this month.
የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ አንድ ሪፖርት እንደሚለው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በዚህ ወር 4.
English
Amharic
The figure includes 5.75 million Ethiopian children.
5 ሚሊዮን ጨምሯል፡፡
English
Amharic
The food crisis in the country is being played down by the Ethiopian government, which has decided to rename famine and starvation as food insecurity”:
የአገሪቱ የረኀብ ቀውስ በኢትዮጵያ መንግሥት ዝቅ ተደርጎ ከመታየቱም ባሻገር መንግሥት የረኀቡን ሥም በመቀየር የምግብ እጥረት” እንደሆነ ገልጧል፡
English
Amharic
According to some inside Ethiopia, NGOs are being warned not to use the words famine, starvation or death” in their food appeals.
ከኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ረኀብ፣ ችጋር ወይም ሞት” የሚሉ ቃላቶችን በምግብ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ እንዳያካትቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
English
Amharic
Neither are they to say that children are dying on a daily basis,” or refer to widespread famine” or say that the policies of the government in Ethiopia are partially to blame.”
በተጨማሪም ሕፃናት በየዕለቱ እየሞቱ ናቸው” ወይም ደግሞ ሰፋ ያለ የረኀብ አደጋ” ወይም የመንግሥት ፖሊሲ ለረኀቡ በከፊል ተጠያቂ ነው” የሚሉ ሐረጎችንም መጠቀም አልተፈቀደም፡፡
English
Amharic
Neither are they allowed to compare the current crisis to the famine of the eighties.”
ይህንን ረኀብ ከ1977ቱ ድርቅ ጋር ማነፃፀር”ም እንዲሁ አልተፈቀደላቸውም፡፡
English
Amharic
Instead, the latest drought in Ethiopia is to be described as food insecurity caused by a drought related to El Nino.”
እንዲሁ ብቻ በኤል ኒኞ ምክንያት የተከሰተ የምግብ እጥረት” በሚል እንዲገልጹ ታዘዋል፡፡
English
Amharic
While the Ethiopian government says that the cause of food insecurity” in the country is drought related to El Nino, Dawit Ayele Haylemari, a graduate student of political science at University of Passau, thinks otherwise:
የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ የተከሰተው የምግብ እጥረት” ኤል ኒኞን ተከትሎ በመጣው ድርቅ ሳቢያ ነው ቢልም ዳዊት አየለ ኃይለማርያም የተባለ በፓሳው ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ግን በተቃራኒው ነው የሚያስበው:
English
Amharic
Many experts relate Ethiopia's cyclical famine with the country's dependence on Rainfed smallholder agriculture, drought, rapid population growth or agricultural market dysfunctions.
ብዙ ባለሙያዎች የኢትዮጵያን የከፋ ረኀብ ዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነ አነስተኛ የአስተራረስ ዘዴ፣ ድርቅ፣ ፈጣን የሕዝብ ዕድገት ወይም የእርሻ ገበያ መውደቅ ጋር ያገናኙታል፡፡
English
Amharic
Although these factors do have significant role in the matter, they tend to hide the critical cause of hunger in the country - lack of rights and accountable government
ምንም እንኳን እነዚህ ነገሮች በጉዳዩ ላይ የላቀ ሚና ቢኖራቸውም፣ በአገሪቱ ያለውን ዋነኛ የችጋር መንስኤ ግን ይሸሽጋሉ - እነዚህም የመብቶች አለመከበር እና ተጠያቂነት ያለበት መንግሥት እጦት ናቸው፡፡
English
Amharic
A historical investigation of famine also identified 30 major famines during the 20th century.
የረኀብ ታሪካዊ ዳራው ሲጠና በ20ኛው ክፍለ ዘመን 30 ትላልቅ ረኀቦች ተከስተዋል፡፡
English
Amharic
All happened in countries led by autocratic rule or that were under armed conflict, four being in Ethiopia Why does autocracy lead to famine?
ሁሉም የተከሰቱት በአምባገነን መንግሥታት ሥር ወይም በትጥቅ ትግል ውስጥ ባሉ አገሮች ውስጥ ነው፡፡ አራቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የተከሰቱት አምባገነንነት ለምን ለረኀብ ይዳርጋል?
English
Amharic
The most fundamental reason is that autocrats often don't care enough about the population to prevent famine.
ዋነኛው ምክንያት አምባገነኖች ረኀብን ለመከላከል በሚያዘጋጅ ሁኔታ ለሕዝባቸው አይጨነቁም፡፡
English
Amharic
Autocrats maintain power through force, not popular approval.
አምባገነኖች ሥልጣናቸውን የሚያስጠብቁት በኃይል እንጂ በሕዝባዊ ይሁንታ አይደለም፡፡
English
Amharic
This argument has been proven true in the case of Ethiopia.
ሙግቱ በኢትዮጵያም ታይቶ እውነትነቱ ተረጋግጧል፡፡
English
Amharic
The food crisis, in the fifth largest economy in Sub Saharan Africa, has become one of the hot topics discussed by Ethiopian netizens online.
ከሰሀራ በታች ካሉት አገራት 5ኛውን ትልቁን ኢኮኖሚ የያዘችው አገር የገጠማት የረኀብ ቀውስ፣ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ የሞቀ መወያያ ሆኗል፡፡
English
Amharic
Adisu Habte took a jab at Ethiopians in the Diaspora talking about the issue on social media while their fellow citizens are dying:
አዲሱ ሀብቴ ዳያስፖራዎች የአገራቸው ዜጎች እየሞቱ ሳለ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማውራታቸውን እንደነውር በመቁጠር በነገር ሸንቁጧቸዋል፡
English
Amharic
Well the hunger continues in Ethiopian while Ethiopians living in Philadelphia continue to do nothing but post on their social media page and have conversation about politics at Dunkin Donuts and at the Hookah lounge Let's not watch as Ethiopians are starving to death.
ፊላደልፊያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምንም ሳያደርጉ ነገር ግን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እና ደንኪን ዶናትስ እና ሺሻ ቤቶች ውስጥ ፖለቲካ ሲያወሩ ኢትዮጵያውያን ግን እየተራቡ ነው ኢትዮጵያውያን በረኀብ ሲሞቱ ዝም ብለን አንይ፡፡
English
Amharic
Yep!
አዎ!
English
Amharic
The 'fast growing' economy in Ethiopia is busted ...
‹በፍጥነት አዳጊው› የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጉዱ ፈላ…
English
Amharic
Yes, drought and hunger in the fastest growing African economy #Ethiopia — P Mimi Poinsett MD (@yayayarndiva) November 28, 2015
አዎ፣ ድርቅ እና ረኀብ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝጋቢዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቷል፡፡ — P Mimi Poinsett MD (@yayayarndiva) November 28, 2015
English
Amharic
While Betelhem Ephrem advises Ethiopians not to politicise the issue:
ቤተልሔም ኤፍሬም ኢትዮጵያውያን ጉዳዩን ፖለቲካ እንዳያደርጉት መክራለች:
English
Amharic
For once lets make this issues about the people who are desperately in need of survival than our political discourse. lets not make a mockery of the people at this time of crisis.
5 ሚሊዮኖች ረኀብ ገጥሟቸዋል የሚለው ውስጥ የቁጥሩ ምንጭ ከየት እንደሆነ ሲጠይቅ ከአዲስ ስታንዳርድ የተሰጠው መልስ:
English
Amharic
Answering to a Facebook user, Anania Sorri, who wanted to know the source of the information that 4.5 million are facing hunger, Addis Standard writes: Dear Anania Sorri - It is widely known that figures in this country are often the results of negotiations between the government and aid agencies (in this case) or the government and financial institutions (in the case of growth).
ውድ አናንያ ሶሪ፣ በሰፊው እንደሚታወቀው ቁጥሮች (በዚህ ጉዳይ) በመንግሥት እና የዕርዳታ ድርጅቶች መካከል (ወይም በዕድገት ጉዳይ) በመንግሥት እና የፋይናንስ ተቋማት መካከል የሚደረግ ድርድር ውጤት ነው፡፡
English
Amharic
But in the face of eminent crop failure in many parts of the country in the coming harvest season, this one doesn't seem to be overly exaggerated.
ነገር ግን በይፋ የታወቀ የምርት ውድቀት በአገሪቱ በተንሰራፋበት በዚህ ወቅት፣ ቁጥሩ የተጋነነ አይመስልም፡፡
English
Amharic
Responding to calls from some Ethiopians that citizens need to pray, Biyya Oromiyaa says:
ዜጎች መፀለይ አለባቸው ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ፣ ቢያ ኦሮሚያ እንዲህ ብሏል:
English
Amharic
How is praying a solution to hunger in Ethiopia?
በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረኀብ ፀሎት እንዴት ነው መፍትሔ የሚሆነው?
English
Amharic
Hungry people need emergency food, and a good agricultural policy with political will and democracy.
የተራቡ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ እና መልካም የግብርና ፖሊሲ ከመልካም የፖለቲካ ፈቃደኝነት እና ዴሞክራሲ ጋር ነው የሚያስፈልጋቸው፡፡
English
Amharic
Hunger has nothing to do with God in Ethiopia, maybe elsewhere.
ረኀብ በኢትዮጵያም ሆነ ሌላ ቦታ ከእግዜር ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም፡፡
English
Amharic
Hunger is created by the combination of regime policy failure, political oppression and climate change.
ረኀብ በስርዓቶች የፖሊሲ ውድቀት፣ የፖለቲካ ጭቆና እና የአየር ንብረት ለውጥ ድምር ውጤት የሚከሰት ነገር ነው፡፡
English
Amharic
So good advice would be to remove the regime than instruct us to pray.
ጥሩ ምክር የሚሆነው ስርዓቱን ማስወገድ እንጂ እንድንፀልይ ማዘዝ አይደለም፡፡
English
Amharic
Fikrejesus Amahazion, a Horn of Africa scholar focusing on African development, human rights and political economy, points to another irony of the current food crisis:
ፍቅረየሱስ አምሀፅዮን የተባለ የአፍሪካ ልማት፣ ሰብኣዊ መብቶች እና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩር የምሥራቅ አፍሪካ ምሁር ደግሞ የረኀብ ቀውሱን በተመለከተ ሌላ አስተዛዛቢ ጉዳይ ጠቁሟል:
English
Amharic
Ironically, while Ethiopia is facing a hunger crisis and making urgent appeals for aid, tonnes of food are actually leaving the country.
ኢትዮጵያ የረኀብ ቀውስ ተጋርጦባት አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እየጠየቀች እያለ ብዙ ቶን ምግብ ከአገሪቷ እየወጣ መሆኑ አስተዛዛቢ ነው፡፡
English
Amharic
This illogical development is due to the fact that the regime in Addis has sold large tracts of arable land to a range of foreign investors and corporations in transactions described as land grabs.”
ይህ የማይገባ ልማት የተፈጠረው ደግሞ አዲስ አበባ የተቀመጠው መንግሥት ትልልቅ ለም መሬቶችን መሬት መቀራመት” እየተባለ በተተቸ መንገድ ለውጭ ኢንቨስተሮች እና ኮርፖሬሽኖች በመቸብቸቡ ነው፡፡
English
Amharic
Reports by rights groups list a plethora of human rights violations, including murders, beatings, rapes, imprisonment, intimidation, and political coercion by the government and authorities.
የመብት ተቆርቋሪዎች ግድያዎች፣ ድብደባ፣ መደፈር፣ እስር፣ ማዋከብ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖን የሚያካትቱ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በመንግሥት እና ባለሥልጣናት እንደተፈፀመ አጋልጠዋል፡፡
English
Amharic
Ethiopia’s hunger crisis is an important humanitarian issue meriting immediate attention and concern.
የኢትዮጵያ የረኀብ ቀውስ አስቸኳይ ትኩረት የሚሻ ሰብኣዊ ጉዳይ ነው፡፡
English
Amharic
In order to fully understand the crisis it is imperative to recognize that while the environment has been an important contributing factor, a range of other structural socio-political and governance dynamics, including corruption, the lack of rule of law or democracy, poor governance, failures in long-term planning, and misplaced national and development priorities have also been highly influential.
ሁኔታውን በጥቅሉ ለመረዳት የአካባቢ ሁኔታ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ቢታወቅም፣ በተጨማሪም ማኅበረ-ፖለቲካዊ እና የአስተዳደር ሁኔታው፣ ሙስና፣ የሕግ የበላይነት እጦት፣ የመልካም አስተዳደር አለመኖር፣ የረዥም ግዜ ዕቅድ ክሽፈት፣ የተሳሳተ ብሔራዊ እና የልማት ትኩረት ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡
English
Amharic
Finally, Paul Dorosh, director at International Food Policy Research Institute's Development Strategy and Governance Division, and Shahidur Rashid, senior research fellow at the institute’s Markets, Trade, and Institutions Division, are hopeful that the drought will not lead to famine:
በመጨረሻም፣ የዓለምዐቀፉ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ተቋም፣ የልማት ስትራቴጂ እና አስተዳደር ክፍል ዳይሬክተር ፖል ዶሮሽ እና የተቋሙ የገበያ፣ ንግድ እና ተቋማት ክፍል የበላይ ተመራማሪ ሻሂዱር ራሺድ ድርቁ ወደ ረኀብ እንደማያመራ ተስፋ ያደርጋሉ:
English
Amharic
The 2015-16 drought and production shortfall need not cause a famine in Ethiopia.
የ2008ቱ ድርቅ እና የምርት መቀነስ በኢትዮጵያ ረኀብ አያስከትልም፡፡
English
Amharic
By heeding the lessons of past famines, the government and the international donor community can help ensure that there is sufficient availability of cereals to supply Ethiopia’s food needs and sufficient transfers in cash and in kind to provide needy households with adequate access to food.
ከቀድሞ ረኀቦች ትምህርት በመቅሰም መንግሥት እና ዓለምዐቀፍ ለጋሽ ማኅበረሰቦች ለሚያስፈልጋቸው የእህል አቅርቦት እና በገንዘብም ይሁን በቁስ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ቀድሞ ማዘጋጀቱን እና ምግብ ለሚያስፈልጋቸው መድረሱን ያረጋግጣሉ፡፡
English
Amharic
Other food security issues will still need to be resolved, including ensuring adequate nutrition for all individuals.
ሌሎች የምግብ ፍላጎት መሟላት እና ተመጣጣኝ ምግብ ለሁሉም ግለሰቦች የመዳረሱ ጉዳይም ይቀረፋል፡፡
English
Amharic
Oromo singer Hawi Tezera.
የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና
English
Amharic
Photo from her official Facebook page. While journalists and bloggers remain the primary targets of state repression in Ethiopia, musicians that don't jive with state propaganda also take the heat.
ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች የመንግሥት አፈና ግንባር ቀደም ተጠቂዎች በሆኑባት ኢትዮጵያ፣ ከመንግሥት ፕሮፓጋንዳ የማይገጥሙ ሙዚቀኞችም ትኩሳቱን እየተቀላቀሉ ነው፡፡
English
Amharic
Hawi Tezera, an ethnic Oromo singer, was reportedly beaten, arrested, released and then rearrested in the space of just seven days by government security forces in connection with her song about ongoing protests in Oromia, a southern administrative region that is Ethiopia’s largest.
ሐዊ ተዘራ፣ የኦሮሞ ዘፋኝ ስትሆን በኢትዮጵያ ትልቁ ክልል ኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ካለው የአደባባይ ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አለሽ በሚል በፖሊስ ተደብድባ ከታሰረች በኋላ ተፈትታ በሰባት ቀን ጊዜ ውስጥ መልሳ በድጋሚ እንደታሰረች ሪፖርት ተደርጓል፡፡
English
Amharic
Two other Oromo singers, who asked to remain anonymous for fear of retribution, told this author over Facebook chat that they have been under intense surveillance since anti-government protests began in the region in November.
ሁለት ሥማቸው ለደኅንነታቸው ሲባል እንዳይገለጽ የፈለጉ የኦሮምኛ ዘፋኞችም፣ ለዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ሕዳር ወር ላይ የአደባባይ ተቃውሞው ከተጀመረ ወዲህ በጥብቅ ክትትል ውስጥ እንደሚገኙ ነግረውታል፡፡
English
Amharic
According to some estimates, over a hundred demonstrators have died in unrest that began after the government made plans for the expansion of the capital Addis Ababa into land inhabited by the Oromo ethnic group, which accounts for almost a third of Ethiopia's population.
አንድ ግምታዊ ስሌት እንደሚያመላክተው፣ የዋና ከተማዋ አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያን ሲሦ ያክል ሕዝብ ያለው የኦሮሞ ብሔር ወደሚኖርበት አካባቢ ለማስፋፋት የተዘጋጀውን የመንግሥት ዕቅድ በመቃወም በተነሳው የአደባባይ ተቃውሞ ከመቶ በላይ ሰልፈኞች ሞተዋል፡፡
English
Amharic
In the last two decades, Oromo singers who gravitate towards political and social activism have been subjected to intimidation, abductions and torture.
ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት፣ ወደ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ አራማጅነት ያደሉ የኦሮምኛ ዘፋኞች ለውክቢያ፣ ጠለፋ እና ስቃይ እየተዳረጉ ነው፡፡
English
Amharic
There are also more musicians-in-exiles among the culturally distinct Oromo group than any of Ethiopia's other major groups.
በኢትዮጵያ ከሁሉም ዋና-ዋና ሕዝቦች በጣም ብዙ ሙዚቀኞች የተሰደዱት የኦሮምኛ ቋንቋ ዘፋኞች ናቸው፡፡
English
Amharic
One of the most recognisable victims of this slow purge was iconoclastic Oromo singer, Ebisa Adugna, who civic activists believe was killed by Ethiopian government forces in 1996.
ከዚህ ቀዝቃዛ ዘመቻ ዕውቅ ሰለባዎች አንዱ ተወዳጁ ኢቢሳ አዱኛ ሲሆን፣ ሲቪል አራማጆች በ1988 የተገደለው በመንግሥት ኃይሎች ነው ብለው ያምናሉ፡፡
English
Amharic
Dawite Mekonen, widely known for streamlining Oromo traditional music with more contemporary styles in the 1990s, went into exile after refusing to perform for soldiers at war front during Ethio-Eritrean war in 1998.
ዳዊት መኮንን፣ በ1980ዎቹ የኦሮምኛ ትውፊታዊ ዜማዎችን ከዘመናዊ ሙዚቃ ጋር እያዋሃደ በመጫወት የሚታወቅ ዘፋኝ ሲሆን፣ ለስደት የተዳረገው በ1990ው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ጦርሜዳ ላሉ ወታደሮች እንዲዘፍን ተጠይቆ ባለመስማማቱ ነው፡፡
English
Amharic
These are just few of the better-known examples of Ethiopia’s repression of Oromo musicians.
እነዚህ ጥቂት በይፋ የሚታወቁ ብቻ የኦሮሞ ሙዚቀኞች ላይ እየደረሰ ያለው አፈና ማሳያዎች ናቸው፡፡
English
Amharic
New wave of censorship?
አዲስ የሳንሱር ማዕበል?
English
Amharic
Musicians of all backgrounds that go against the government line find it difficult to get a gig or airtime on Ethiopia's radio stations.
በኢትዮጵያ ከመንግሥት መሥመር በተቃራኒ የሚቆሙ ሙዚቀኞች የኋላ ማንነታቸው ማንም ይሁን ምን በኢትዮጵያ ሬድዮ ጣቢያዎች የአየር ሰዐት ማግኘትም ይሁን በመድረክ ላይ ሥራዎቻቸውን ማቅረብ ይቸገራሉ፡፡
English
Amharic
One example of this trend is the last-minute cancellation last year of two concerts featuring Teddy Afro, a prominent Amharic singer and song writer.Teddy has a great popular appeal and is widely known as the most successful musician in Ethiopia.
ባለፈው ዓመት ሊያቀርባቸው የነበሩ ሁለት ኮንሰርቶች በመጨረሻዋ ደቂቃ የተሰረዙበት ዕውቅ የአማርኛ ዘፋኝ እና የዜማ ጸሐፊ ቴዲ አፍሮ አንዱ ምሳሌ ነው፡፡ ቴዲ ትልቅ ሕዝባዊ ተቀባይነት ያለው እና በእጅጉ ስኬታማ መሆን የቻለ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው፡፡
English
Amharic
Teddy, who was released from imprisonment on hit and run charges he always denied in 2009, said his team was refused permission to hold the concerts scheduled for last September, without speculating as to why.
ቴዲ፣ እሱ እስካሁን ባላመነው ገጭቶ የማምለጥ ክስ ታስሮ በ2001 ከተፈታ በኋላ ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ ሊያቀርባቸው የነበሩ ኮንሰርቶች፣ ምክንያቱ ሳይገለጽ ፈቃድ መከልከላቸውን ተናግሯል፡፡
English
Amharic
It seems most likely the cancellations are part of a continuing government campaign against the musician since his release of songs critical of the regime in 2005, three years before he was imprisoned.
የኮንሰርቶቹ መሰረዝ ቴዲ ከመታሰሩ ሦስት ዓመት ቀደም ብሎ፣ በ1997 ከለቀቃቸው መንግሥትን የሚተቹ ዘፈኖች በኋላ የቀጠለ የአፈና ዘመቻ ይመስላል፡፡
English
Amharic
However, censorship is noticeably harsher as regards the Oromo, Ethiopia's single largest ethnic group, which is viewed as a threat by a government packed with politicians from the northern Tigray minority.
ይሁን እንጂ አፈናው በኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ ባለውና ከሰሜናዊው የሕዳጣን ትግራይ ክልል ውስጥ ለወጡት የመንግሥት ፖለቲካ አመራሮች ተቀናቃኝ ይሆናሉ የሚባሉት ኦሮሞዎች ዘፋኞች ላይ እንደሚበረታ ይስተዋላል፡፡
English
Amharic
According to reports at least 17 Oromo singers whose lyrics show nationalistic tendencies were banned from air waves in December 2015 by the Ethiopian Broadcast Authority.
አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ግጥሞቻቸው የብሔርተኝነት አዝማሚያ” አላቸው ተብለው የሚታሰቡ ቢያንስ 17 የኦሮሞ ዘፋኞች ዘፈኖችን እንዳይሰራጩ አግዷል፡፡
English
Amharic
Oromo singers often produce music that articulates strong pride in their national and cultural heritage, whether through lyrics or the incorporation of traditional instruments and melodies.
የኦሮሞ ዘፋኞች ብዙውን ጊዜ ብሔራዊ ማንነትን እና ባሕላዊ ቅርሶችን የሚያወድሱ ዜማዎች በግጥሞች ወይም በባሕላዊ መሣሪያዎች እና ዜማዎችን በመጠቀም ይጫወታሉ፡፡
English
Amharic
The latest ban has encompassed songs that appear to be far from overtly nationalistic, including the songs of the two musicians the author interviewed for this piece.
የቅርብ ጊዜ እገዳው ደግሞ ብሔርተኛ ከሆኑ ሙዚቃዎችም ውጪ ሆኗል፡፡ ይህ እገዳ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ድምፃውያን ዘፈኖችን ይጨምራል፡፡
English
Amharic
This signifies a clampdown on even moderate forms of cultural self-expression.
ይህ የሚያሳየው መደበኛ የባሕላዊ መገለጫዎችንም መንግሥት ማፈን መጀመሩን ነው፡፡
English
Amharic
A counterproductive policy
የማጨናገፍ ፖሊሲ
English
Amharic
According to academic Michael Shawn Mollenhauer, who wrote his doctoral dissertation on the topic of censorship of Oromo culture in Ethiopia, the current government uses Oromo musicians to present a facade of cultural diversity while systematically imprisoning and intimidating independent singers.
ማይክል ሻውን ሞለንሀወር የተባሉ ምሁር ለዶክትሬት ዲግሪያቸው ሟሟያ በሠሩት ጥናት ላይ የኦሮሞ ባሕል ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚደረግ ሳንሱር በጻፉት ጽሑፍ፣ አሁን ያለው መንግሥት የሚፈልገውን ዓይነት የባሕል ብዝኃነት የሚያሳዩለትን የኦሮሞ ሙዚቀኞች እየተጠቀመ ነጻና ገለልተኛዎቹን ዘፋኞች ግን በዘዴ ለውክቢያ እና እስር ይዳርጋቸዋል፡፡
English
Amharic
Hawi Tezera's story is an indicator that the state's grip on any form of freedom of expression is getting ever-tighter, with controls over music reaching a new low.
የሐዊ ተዘራ ታሪክ መንግሥት የደረሰበት ራስን የመግለጽ ነጻነትን የማፈን ደረጃ ምን ያክል ይበልጥ እንደጠበቀ እና ሙዚቃንም ጭምር እስከማፈን እንደወረደ ማሳያ ነው፡፡
English
Amharic
However, the crackdown is not having the desired effect.
ነገር ግን፣ እርምጃው የሚፈለገውን ውጤት እያመጣ አይደለም፡፡
English
Amharic
If anything, music censorship has helped strengthen Oromo nationalism.
የሙዚቃ ሳንሱሩ የፈየደው ነገር ቢኖር የኦሮሞ ብሔርተኝነትን መጨመሩ ነው፡፡
English
Amharic
The overwhelming majority of Oromos already felt that their identity was being attacked unjustly, and the intensification of state harassment against a background of growing political unrest is tipping them over the edge.
ብዙኃን ኦሮሞዎች አሁን ማንነታቸው አላግባብ እንደተጠቃ ይሰማቸዋል፤ የፖለቲካ ተቃውሟቸው ላይ በመንግሥት እየተሰነዘረ ያለው ጥብቅ ጥቃትም ብዙዎቹን ወደጠርዝ እየገፋቸው ነው፡፡
English
Amharic
This story was commissioned by Freemuse, the leading defender of musicians worldwide, and Global Voices for Artsfreedom.org.
ይህ ጽሑፍ በዓለማችን ላሉ ሙዚቀኞች ቀዳሚ ተሟጋች በሆነው በፍሪምዩዝ እና የዓለም ድምፆች ለጥበብ ነጻነት ኮሚሽን ተደርጓል፡፡
English
Amharic
The article may be republished by non-commercial media, crediting the author Endalk, Freemuse and Global Voices and linking to the origin.
መጣጥፉ በሌሎች የንግድ ባልሆኑ ብዙኃን መገናኛዎች የጸሐፊው ሥም እንዳልክ፣ ፍሪምዩዝ እና የዓለም ድምፆች ተጠቅሰው እና የመጀመሪያው ጽሑፍ ሊንክ ተያይዞ ሊታተም ይችላል፡፡
English
Amharic
A viral detergent commercial showing a black man being stuffed into a washing machine by his Chinese girlfriend and washed into a handsome, light-skinned Chinese man sparked outrage outside China this week for its overt racism.
ከፍተኛ ስርጭት ያገኘው አንድ ጥቁር ሰው በሴት ፍቅረኛው ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ገብቶ ታጥቦ” ሲወጣ መልከመልካም፣ ነጭ ቆዳ ያለው ቻይናዊ ሰው የሆነ፣ የማጠቢያ ኬሚካል ማስታወቂያ ከቻይና ውጪ ያሉ ሰዎችን በዘረኛነቱ አስቆጥቶ ሰንብቷል፡፡
English
Amharic
The detergent company, Qiaobi, quickly apologized and withdrew the commercial, but its public statement accused foreign critics of overreacting.
የማጠቢያ ኬሚካል አምራቹ ኩባንያ፣ ኪያኦቢ ወዲያው ይቅርታ ጠይቆ ማስታወቂያውን አንስቷል፡፡
English
Amharic
Many Chinese web users supported their defensive stance, saying the ad only reflects cultural differences rather than racism and proclaiming that it is impossible for Chinese to be racist toward black people.
ብዙ የቻይና ዜጎችም በኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያው የባሕል ልዩነትን ከማሳየቱ በቀር ምንም ዘረኝነት የለውም፤ የቻይና ሕዝብ በጥቁር ሕዝብ ላይ ዘረኛ ሊሆን አይችልም በማለት ኩባንያውን ደግፈውታል፡፡
English
Amharic
Outside China, people may find this ad racist.
ከቻይና ውጪ፣ ሰዎች ይህን ማስታወቂያ እንደዘረኝነት ሊያዩት ይችላሉ፡፡
English
Amharic
But in China, it is different.
በቻይና ግን የተለየ ነው፡፡
English
Amharic
It is just an ad.
በቃ ማስታወቂያ ብቻ ነው፡፡
English
Amharic
Each country has its own culture, and viewpoints are also difference.
ሁሉም አገር የራሱ ባሕል አለው፤ አመለካከቶችም ይለያያሉ፡፡
English
Amharic
The company can produce another ad and stuff a hairy white guy into washing machine.
ኩባንያው ፀጉራም ነጭ ሰውዬ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ሲገባ መሥራት ይችላል፡፡
English
Amharic
Tell the Americans that we discriminate against blacks and whites.
አሜሪካኖቹን ነጭ እና ጥቁሮችን እንደምናገል ንገሯቸው፡፡
English
Amharic
Are you satisfied?
ይህ ያረካችኋል?
English
Amharic
There is no problem with the ad. Please don't import the political correctness about racism to China.
ማስታወቂያው ችግር የለበትም፤ የፖለቲካ ትክክለኝነትን ጉዳይ በዘረኝነት ሥም እባካችሁ ወደቻይና አታምጡብን፡፡
English
Amharic
Yellow-skinned people have never enslaved black-skinned people, have never forced them into labor or sold them on the open market. don't have the Ku Klux Klan or racial segregation.
ቢጫ ቆዳ ያላቸው ሕዝቦች፣ ጥቁር ቆዳ ያላቸውን ሕዝቦች ቅኝ ገዝተው አያውቁም፤ ለጉልበት ሥራ አላስገደዷቸውም፤ በክፍት ገበያ አልሸጧቸውም፡፡
English
Amharic
Go after your real enemy.
እውነተኛ ጠላታችሁን እዛው ፈልጉ፡፡
English
Amharic
Only when white people discriminate against black people is it racism.
ዘረኝነት ነጮች ጥቁሮችን ሲያገሏቸው ብቻ ነው፡፡
English
Amharic
The discrimination against black-skinned people by yellow-skinned people is just cultural difference.
ቢጫ ቆዳ ያላቸው ጥቁር ቆዳ ያላቸውን ካገለሉ የባሕል ልዩነት ነው፡፡
English
Amharic
Whites are born racist.
ነጮች ናቸው ዘረኛ ሆነው የሚወለዱት፡፡
English
Amharic
To prevent the avalanche of negative press from spinning into a diplomatic crisis, Foreign Ministry spokesman Hua Chunying stressed that spot was an isolated incident and that the Chinese are good brothers with African countries.
የፕሬስ አቤቱታውን ጎርፍ ለማስቆም፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሕዝብ ግንኙነት ሁዋ ቹኒንግ ማስታወቂያ ጠቅላላ ሁኔታውን የሚገልጽ ሳይሆን የተለየ ክስተት እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረው፤ ቻይኖች ከአፍሪካ አገሮች ጋር መልካም ወንድሞች” ናቸው ብለዋል፡፡
English
Amharic
Though the commercial is indeed an isolated production, the denial of racism against black people existing in China and the claim that the Chinese are nothing but good brothers to black people are inaccurate, two anthropology students argued on investigative journalism platform The Initium.
ምንም እንኳን ማስታወቂያው ብቸኛ አጋጣሚ ቢሆንም ቻይኖች ለአፍሪካውያን መልካም ወንድሞች” ናቸው በሚል ዘረኝነቱን እንዳለ መካዱ ግን ትክክል አይደለም በማለት ሁለት የአንትሮፖሎጂ (የባሕል ጥናት) ተማሪዎች ተሟግተዋል፡፡
English
Amharic
But, they said, such racism has become so normalized that many Chinese fail to even see it.
ነገር ግን፣ ይህ ዓይነቱ ዘረኝነት ከመለመዱ የተነሳ ቻይኖች ማስተዋል እንዳይችሉ ሆነዋል፡፡
English
Amharic
The Chinese Communist Party, after taking control of China in 1949, did attempt to unite with their oppressed African brothers against Western imperialism.
በ1949 ሥልጣን ከያዘ በኋላ ከተጨቆኑ የአፍሪካ ወንድሞቻቸው” ጋር በምዕራባውያን ኢምፔሪያሊዝም ላይ ለመተባበር ሞክረዋል፡፡
English
Amharic